የደንብ ማስከበር አባላት በዛሬው እለት በዓሉ በሰላም እንዲከበርና የኮሪደር ልማቱ ጉዳት እንዳይደርስበት ላሳዩት የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቁ
የደንብ ማስከበር አባላት በዛሬው እለት በዓሉ በሰላም እንዲከበርና የኮሪደር ልማቱ ጉዳት እንዳይደርስበት ላሳዩት የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቁ
11/05/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ ከተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት በተጨማሪ በከተማው የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑ ገለፁ።
የባለስልጣኑ አመራርና አባላት በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት እየተከበረ የሚገኘው የአደባባይ በዓል የሆነውን የጥምቀት በዓልን በከፍተኛ ሁኔታ እያስተባበሩ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ከሌሎች የፀጥታ ጥምር ሀይሎች ጋር በመሆን
እያስከበሩ መሆኑ አባላቱ ገልፀዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ ማስከበር አመራርና አባላት በዛሬው እለት በዓሉ በሰላም እንዲከበርና የኮሪደር ልማቱ ጉዳት እንዳይደርስበት ላሳዩት የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ አመስግነው ሌሎች ታቦታትም ወደ መንበረክብራቸው እስኪመለሱ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በክብረ በዓሉ የጠፍ ህፃናትን ከወላጆቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው በማገናኘትና አቅመ ደካማ አባቶችና እናቶች በመደገፍ አስተዎፆኦ ሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ማድረጋቸው ተመላክቷል።
የበዓሉ ታዳሚዎችና የዕምነቱ ተከታዮች አባላቱ ለሚያደርጉት መልካም ተግባር አመስግነው ይህ መልካም ተግባራቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
መረጃው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments