
ባለስልጣኑ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ደንበኞች አያያዝ ላይ ስልጠና ሰጠ
ህዳር 26/2017
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ጥናት ዳይሬክቶሬት ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በደንበኞች አገልግሎት አስጣጥ እና አያያዝ ዙሪያ ለማእከል እና ክፍለ ከተማ ሲቪል ሰራተኞች በባለስልጣኑ መሰብሰባያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻ ንግግራቸው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከከተማ አስተዳደሩ የተጣለበት ህዝብን በቅንነት በታማኝነት አገልግሎትን በጥራት የመስጠት ኃላፊነትን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም እንደመሆኑ እንደነዚ አይነት ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ብለዋል::
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የቅድመ መከላከል እና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኮ/ር አህመድ መሀመድ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ጤናማ ለማድረግ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ትልቁን ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል::
ስልጠናው ከትምህርት ተቋማት ከምናገኘው እውቀት ባሻገር እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው ስራችንን ብቁ እና ተወዳዳሪ ከማድረግ አኳያ ትልቅ አስተዋፆ እንዳለው መረዳት እንደሚገባ ገልፀው ከዛሬው ስልጠና ትምህርት ወስዳችሁ ቅን ታዛዥ ታማኝ የሆነ አገልጋይ እንድትሆኑ መልክቴን አስተላልፋለው በማለት የመክፈቻ ንግግራቸውን አስተላልፈዋል::
የአገልግሎት አሰጣጥ እና የደንበኛ አያያዝ ስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ምንነት, ስለ ተገልጋይ ስነ-ልቦና አረዳድ ክህሎት, ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እንዴት ማዘመን ይቻላል,በሚል አቅርበዋል።
ስልጠናው የደንበኛን ቅሬታ ማስተናገጃ መንገዶችን በትክክል ከመረዳት እና የመፍቻ መንገዶች ጋር በተያያዘ እንዲሁም ስለ አጠቃላይ ፅንሰ ሀሳቡ በማንሳት የተቋሙን ባህሪ መሰረት በማድረግ ተሰጥቷል ::
በመጨረሻም ተሳታፊዎችም የመንግስት ተቋም የራሱ የሆነ የአሰራር ስርአት እና የህግ ማዕቀፍ ያለው በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡ ያንን ማዕከል ያደረገ እንዲሆንና ሰራተኞችም ስራችን በጥራት በመከወን እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ይገባናል የሚሉ ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል::
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም የባለስልጣኑ የኦንላይን ቅሬታ መቀበያ ፎርም ለማግኘት የተዘጋጀ ሊንክ እና አተገባበር በተመለከተ በተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ካሳሁን ተዋውቋል::
ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሀመድ ስልጠናው መሰጠቱ በቀጣይ ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እና ስልጠናው ወደ ተግባርም መቀየር እንደሚያስፈልግ ተገንዝበን የአገልግሎት አሰጣጣችንን ልናሻሽል ልናዘምን እንደሚገባ ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments