የሰው ኃይል መረጃ አያያዝ የሰለጠኑ ባለሙያዎች የፅህፈት ቤቶቻቸው ሰራተኞች መረጃ በዘመናዊ የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባ ተገለፀ
የሰው ኃይል መረጃ አያያዝ የሰለጠኑ ባለሙያዎች የፅህፈት ቤቶቻቸው ሰራተኞች መረጃ በዘመናዊ የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባ ተገለፀ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለክፍለ ከተማ የሥራ አስተባባሪዎች፣ ለሰው ኃይል ባለሙያዎች እና ለጥሪ ማዕከል ኦፊሰሮች "የመረጃ ምንነት፣ አስፈላጊነት ፣ ባህርያት እና ችግሮች " በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨጫ ስልጠና መሰረት የተቋማቸው መረጃ በዘመናዊ የመረጃ ቋት ማደራጀት እንደሚገባቸ ተገለፀ።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ አንድ መረጃ ጥራት አለው የሚባለው ወቅታዊ፣ ምሉዕ፣ ትክክለኛ፣ ወጥ እና ተደራሽ ሲሆን ብቻ መሆኑን በመገንዘብ መረጃዎች ወቅታዊ፣ የተሞላ ፣ ትክክለኛና ወጥ እንዲሆኑ በማድረግ መረጃ መዛባት ምክንያት የሚፈጠሩ ስህተቶችን መቀነስ እንደሚገባ ገልፀዋል ።
የስልጠናው ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ የስልጠናው ዓላማ በክፍለ ከተማዎች እና በወረዳ ደረጃ የሚገኙትን አጠቃላይ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የሰው ኃይል መረጃ አያያዝ ጋር ያሉ መሰረታ ችግሮችን በመቅረፍ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ማዘመንና ጥራቱን ማሻሻል እንደሆነ ገልጸዋል።
እያንዳንዱ የሥራ ክፍል ጥራቱን የጠበቀና በዘመናዊ የመረጃ ቋት የተደራጀ መረጃ በመያዝ ለተቋሙ ስኬትና ለከተማችን ዕድገት የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ በስልጠናው ተገልጿል::
በቀረበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ዙርያ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments