የባለስልጣኑ የመማክርት ካውንስል 1ኛ ጠቅላላ ጉ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የመማክርት ካውንስል 1ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

የባለስልጣኑ የመማክርት ካውንስል 1ኛ ጠቅላላ ጉባዔ   ተካሄደ
                   10/6/2018 ዓ.ም
                **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመማክርት ካውንስል የ2018 በጀት አመት 1ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን የካውንስሉ እና የተቋሙ አመራሮች በተገኙበት  አካሂዷል።

በጠቅላል ጉባኤው  መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባለስልጣኑ  ከተማዋን ንፁህ ፣ ፅዱና ከማንኛውም የደንብ ጥሰቶች የፀዳች ከተማ ለማድረግ በርካታ ሀላፊነት ተሰጥተውት  በመስራት ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ አገልጋይና የተገልጋይ ተግባቦት ሲኖራቸው  ስራዎች እንደሚሳለጡና ለዚህም የመማክርት ካውንስል ተጠናክሮ  መቀጠል ለባለስልጣኑ  ትልቅ ግብዓት  እነደሚሆን  አስገንዝበዋል ።

በጉባኤው የጠቅላላ ጉባዔውን የካውንስሉ የ6 ወራት ሪፖርት፤ በባለስልጣኑ ክፍለ ከተሞች ፅ/ቤቶች  የተደረገ የድጋፍና ክትትል ሪፖርት በማቅረብ እና የተጓደሉ  የካውንስል የስራ አስፈፃሚና አባላት በመተካት ስራ ተከናውኗል።

የጠቅላላ ጉባዔ  ሪፖርት የ1ኛ ጉባዔው  በሰብሳቢ ሻንበል መኮንንት ነጋሽ  የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ  በዝግጅት ምዕራፍ የተካሄዱ ተግባራት፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ፤ የመታደደርያ ደንብ ስለመዘጋጀቱ ፤ በአገልግሎት ሰጭ እና በተገልጋይ ግንኙነት ላይ ስለተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በመድረኩ በተመረጡ 5 ክፍለ ከተሞች የተደረገ የድጋፍና ክትትል ሪፖርት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር  ፕሬዝዳንትና የባለስልጣኑ የመማክርት ካውንስል አባል የሆኑት ወ/ሮ እናታለም እንዳለ አቅርበዋል፡፡

በሪፖርቱ የክፍለ ከተሞች የመማክርት ካውንስ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፤የስራ  አስፈፃሚ አባላት ስለመመረጡ ፤እቅድ ስለመዘጋጀቱ፤ የመመክርት ካውንስል አባለት ከሁሉም አደረጃጀት ስለመዋቀራቸው  በመሳሰሉት መስፈርቶች ክትትልና ድጋፉ መከናወኑን  ተመላክቷል፡፡

የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በማጠቃለያ ንግግራቸው በመማክርት ካውንስል ከተቋቋመ ጀምሮ የነበሩ የስራ እንቅስቃሴዎች  የሚበረታቱ መሆኑ ገልፀው ለሚያጋጥሙ ችግሮች በጋራ መፍትሄ በመስጠት መልካም አስተዳደር ለማስፈን እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡


በመጨረሻም በተገደሉ   የመማክርት ካዉንስል ስራ አስፈፃሚና አባላት በማተካካት   በቀረቡ የጠቅላላ ጉባዔው አጀንዳዎች ዙርያ ከተሳታፊዎች አስተያትና ጥያቄዎች ተነስተው በተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ከመድረክ ምላሽ   ተሰጥቶ ጉባኤው ተጠናቆል ፡፡

መረጃው፦ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments