
በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አከባቢ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቶች የሚያስተጓጉሉ አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ ተወስደ
በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አከባቢ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቶች የሚያስተጓጉሉ አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ ተወስደ፡፡
ህዳር 26/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በዛሬው በሰጡት መግለጫ፥ የጫት ቤቶችና ፔንሲዮን ቤቶችን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት በፈጸሙ 879 የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል።
አዋኪ ድርጊት በፈፀሙ በ184 ጫትና ሺሻ ቤቶች፣ 112 ግሮሰሪ፤ አረቄና ጠጅ ቤቶች፣ 48 ግሮሰሪ መጠጥ ቤቶች፣ 12 ፔንሲዮን ቤቶች፣ 120 ፑል ማጫወቻ ቤቶች፣ የድምፅ ብክለት ያለባቸው ሙዚቃ ቤቶችና ቪዲዮ ቤቶች 122 እንዲሁም 171 ሌሎች የንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስረድተዋል።
እርምጃ የተወሰደው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ ለማድረግ እንደሆነም የቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል ።
እርምጃው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ትምህርት ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ፣ደንብ ማስከበር ባለስልጣንና ከፓሊስ አባላት ጋር የጋራ ግብረ ሃይል በማቋቋም በተደረገው ጥናት የተሰራ ኦፕሬሽን እንደሆነም ተገልጿል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments