ባለስልጣኑ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል "አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሄደ
ባለስልጣኑ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል "አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሄደ
የካቲት 10/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል የባለስልጣኑ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በውይይት መድረክ አከበረ።
በመድረኩ ላይ የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ የዓድዋን ታሪክና ወቅታዊውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ የሚያስተሳስር ሰነድ አቅርበዋል።
በሰነዱ ዓድዋና ብሔራዊ ጥቅም፣ ለከተማ ብልጽግና የዓድዋ መንፈስ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልጽግና፣ ለዲሞክራሲያዊ ጽናትና ለፍትሀዊ ምርጫ ያለውን ፋይዳ፣ ኃላፊነትን መወጣት ፣ የስነ-ምግባርና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቆራጥነት መታገል የሚሉ ነጥቦች ተካተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ሰራተኞችና አመራሮች በበኩላቸው፤ ሉዓላዊነታችንን ለማስጠበቅና እራስን ከተረጂነት ለማላቀቅ በጋራ መቆም እንደሚገባ ገልጸው በተለይም አሁን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ከድሉ ጋር በማያያዝ፣ ግልጽና ዲሞክራሲያዊ ምርጫን በማካሄድ ለትውልድ የሚተርፍ አሻራ በማኖር "ዳግም ዓድዋን" መፍጠር ይገባል ብለዋል።
መድረኩ የተጠናቀቀው የዓድዋ ድልን ታሪክ ወደ ተግባር በመቀየር፣ ለከተማችን ሰላምና ደንብ መከበር በቁርጠኝነት ለመስራት ቃል በመግባት ነው።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments