የባለስልጣኑ ስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ2018ዓ.ም 6ወር አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ
የባለስልጣኑ ስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ2018ዓ.ም 6ወር አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ። በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ የተወከሉ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
በግምገማው የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦችም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በሚመለከት ባለፉት 6 ወራት በ9ኙ የደንብ መተላለፍ አይነቶች፣ በመመሪያዎችና በአዋጆች ዙሪያ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል። ትምህርቱ በመድረኮች፣ በቤት ለቤት ቅስቀሳ እና በ"ቡና ጠጡ" ፕሮግራሞች አማካኝነት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መድረስ ተችሏል።
በመድረኩም የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን፤ የ6 ወር አፈጻጸሙንና የቀጣይ ወራት ስራዎችን የያዘ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም በሪፖርቱ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት፣ በቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራት በጋራ በመረባረብ የታቀዱ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments