ባለስልጣኑ በትውልድ የስነምግባር ግንባታና ሙስና...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በትውልድ የስነምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል በተመለከ ለተባባሪ አካላት/FOCAL PERSON/ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በትውልድ የስነምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል  በተመለከ ለተባባሪ አካላት/FOCAL PERSON/ስልጠና ሰጠ

             12/6/2018 ዓ.ም
           **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ለማዕከል ባለሙያዎች ፣ ከ11 ክፍለ ከተማ እና ከ119 ወረዳ ለተውጣጡ ተባባሪ አካላት /FOCAL PERSON / ''በትውልድ ስነምግባር ግንባታና ሙስናን መከላከል የተባባሪ አካላትና የባለሙያው ሚና '' በሚል እርዕስ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በባለስልጣኑ የስነምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሪክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ የተሰጠ ሲሆን በስነምግባር መመርያና ውጤት፣ ሰለ ሙስና መከላከል ጥቅሞች እና እንደ ተቋም በክፍተት የሚታዮ የሙስናና የስነ ምግባር ችግሮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው ተሰጥቷል ።

ከስነ-ምግባርና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ በመቅረፍ ከስነምግባር ችግሮች የፀዳ አሰራር መፍጠር እንደሚገባ በስልጠናው  ተመልክቷል።

ከሰልጣኞች ጋር  እንደ ተባባሪ አካላት ብልሹ አሰራር ከመዋጋት አንጻር መሰራት ያለባቸው ተግባራት ምንድናቸው እንዲሁም ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠርስ ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል በሚሉና ተያያዥ ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።

በስልጠናው ማጠቃለያ የተገኙት የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ  የተባባሪ አካላት /FOCAL PERSON/ ሚና ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ የስነምግባር እና የብልሹ አሰራር ግደፈቶች ሲያስተውል በማስተካክል፣ በማረም ፣ ግንዛቤ በመፍጠር እና ተጠያቂ አካለትን እንዲጠየቁ በማድረግ ከባለስጣኑ ጋር ተግባቦት ፈጥሮ የተሰጠውን ተልዕኮ ማስፈፀም የሚችል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል ።

በመጨረሻም  ለተሳታፊዎች ለመወያያነት በቀረቡ ነጥቦችና በተሰጠው ስልጠና ዙርያ ሀሳብ አስተያየት ተነስተው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments