አገልግሎት አሰጣጥ ሰውን ከፍ ያደረገ ፣ ህግን የተከተለ ጊዜና ሀብት ያከበረ ፣ እምነት የሚፈጥር መሆን አለበት"ዶ/ር ሙሉጌታ አየለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት መምህርና ተመራማሪ
"አገልግሎት አሰጣጥ ሰውን ከፍ ያደረገ ፣ ህግን የተከተለ ጊዜና ሀብት ያከበረ ፣ እምነት የሚፈጥር መሆን አለበት"ዶ/ር ሙሉጌታ አየለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት መምህርና ተመራማሪ
16/06/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ከተቋሙ ውጪ የሆነ እንግዳ በመጋበዝ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡
የዕለቱ የወርቃማ ሰኞ እንግዳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ተቋም መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ሙሉጌታ አየለ የመንግስት አገልግሎት እና የዜጎች ተሳትፎ ለሀገር ብልጽግና በሚል የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል ።
የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሰውን ከፍ ያደረገ ፣ ህግን የተከተለ ጊዜና ሀብት ያከበረ ፣ እምነት የሚፈጥር አገልግሎት ማቅረብ እንደሆነ በሰነዱ ተገልጿል ።
ዜጎች በልማት ስራዎች ላይ ሃሳብ በመስጠትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሀገር ባለቤት ሊሆኑ እንደሚገባ ዶ/ር ሙሉጌታ ገልጸዋል።
አክለውም ብልጽግና ከመንግስት ብቻ የሚጠበቅ ሳይሆን መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን ሲፈጥርና ዜጎች በኃላፊነት ስሜት ሲንቀሳቀሱ የሚመጣ የጋራ ውጤት መሆኑንና የመንግስት አገልግሎት ሲዘምንና የዜጎች ተሳትፎ ሲጎለብት፣ የሀገር ብልጽግና የማይቀር መሆኑን ገልጸዋል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ አገልግሎት ስንሰጥ ዝቅ ብለን የተገልጋዩን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ ፍጹም ዲስፕሊን በመላበስ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም በየጊዜው እየተሻሻለና እያደገ በርካታ እውቀት እየተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል ።
አክለውም የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ተገልጋዮችን ክብር በመስጠት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ለስራዎች ስኬት እንዲሁም ተቋምን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments