በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካል ዳይናሚክስ ፈተና እና ተስፋ ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካል ዳይናሚክስ ፈተና እና ተስፋ ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
16/06/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካል ዳይናሚክስ ፈተና እና ተስፋ ለኢትዮጵያ በሚል የግንዛቤ ማስጨበጫ ለማዕከሉ ሰራተኞች ሰጥቷል ።
በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካል ዳይናሚክስ ፈተና እና ተስፋ ለኢትዮጵያ በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ተቋም መምህርና ተመራማሪ በሆኑት ዶ/ር ሙሉጌታ አየለ ቀርቧል።
የአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ወቅት የዓለም ኃያላንና የቀጠናው ሀገራት ፍላጎት የሚያልብበት የፖለቲካ ትኩሳት ሆኗል በዚህ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ኢትዮጵያ የገጠሟት ፈተናዎች እና ከፊቷ ያሉ ተስፋዎች ምንድን ናቸው የሚሉት በሰነዱ በዝርዝር ቀርቧል።
የአፍሪካ ቀንድ ተለዋዋጭ እና ለግጭት የተጋለጠ አከባቢ ቢሆንም በዓለም ላይ ካሉት ዋናዎቹ የጂኦ ስትራቴጂክ ክልሎች አንዱ እንደመሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፉክክሮች እያገረሸ መምጣቱንና ኢትዮጵያም በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የፉክክር ተጽዕኖ ውስጥ መግባቷ የማይቀር ነው ።
ኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ የኢኮኖሚ እና የንግድ ብቻ አለመሆኑንና የደህንነት ጉዳይ መሆኑንን ባህር መዳረሻ ያለው ሀገር በአለም ፖለቲካ ላይ የተለየ ሚና እንደሚጫወት ዶ/ር ሙሉጌታ ተናግረዋል ።
የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ተለዋዋጭ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ የምትከተለው ጥንቁቅ የዲፕሎማሲ አካሄድና የቀጠናዊ ትስስር ራዕይ ለቀጣይ ብልጽግናዋ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments