ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን በዲጂታል መንገድ ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ የዜጎች ተሳትፎ/Citizen Engagment/ ቴክኖሎጂ አስተዋወቀ
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን በዲጂታል መንገድ ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ የዜጎች ተሳትፎ/Citizen Engagment/ ቴክኖሎጂ አስተዋወቀ
27/06/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎች ለመከላከልና የህብረተሰብ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ/Citizen Engagment/ EFP app)ቴክኖሎጂ ለማስጀመር የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት ለሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የተግባር ስልጠና ሰጥቷል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከተማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና ፣ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ እንዲሁም የቱሪስት መስብ በመሆኗ ውብና ጽዱ እንድትሆን የመጠበቅና የማስቀጠል ሰፊ ተልዕኮ የተሰጠን እንደመሆኑ በርካታ ተግባራቶች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ይህንኑ ተግባር ለማስቀጠል አቅማችንን ከወቅቱ ጋር እየገነባን የከተማችንን እድገት በሚመጥን መልኩ ስማርት ቢሮ በመገንባት ስራወችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ ተቋሙ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
አክለውም የነጻ ስልክ መስመር ስርዓቱን በማዘመን ወደ ስራ መገባቱንና የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFP app) ተግባራዊ መድረጉ ተቋሙ ራሱን እያዘመነ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ነው ይህ ቴክኖሎጂ የደንብ መተላለፎችንና ወንጀል መከላከል የጸጥታ ስራን ወደ ዲጂታል በማሸጋገር፣ የከተማችንን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚደረገውን ጉዞ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደምሴ ይልማ ስማርት ሰላሟ የተጠበቀ ከተማ እንዲኖረን ስራዎቻችንን ዲጅታል ማድረግና በቴክኖሎጂ ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን ደንብ ማስከበር በመገንዘብ እያከናወነ የሚገኘው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል ።
የየዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFP app) አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከሁለት ዓመት አልፎታል በዚህ ጊዜያቶች በርካታ የህብረተሰብ ክፍል እየተጠቀመበት የሚገኝ ሲሆን መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላል በሆነ መልኩ የተቀረጸ ስለሆነ ፣ ተጠቃሚዎች በስማርት ስልኮቻቸው ላይ በመጫን በቀላሉ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ኮማንደር ደምሴ አስተውቀዋል ።
መተግበሪያው ፖሊስ የሚሰራቸው ስራዎች ከማቅለል በተጨማሪ ዜጎች ፈጣንና ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።
በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFP app) የግንዛቤ ማስጨበጫና የተግባር ስልጠና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ዶክተር ገመቹ ሰጥተዋል ።
የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFP app) ለአጠቃቀም ቀላል ሲሆን ተጠቃሚዎች ካሉበት ቦታ ሆነው የስማርት ሞባይል ስልኮቻቸው በመጠቀም መረጃ መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን አሰልጣኙ ገልጸዋል ።
መተግበሪያው የህዝብ ተስትፎ ያረጋግጣል ፣ ቴክኖሎጂ የሚጠቀምና የሰለጠነ የጸጥታ አካላት ያፈራል እንዲሁም የተሟላ የዜጎች ደህንነት የማስጠበቅ አገልግሎት ይሰጣል ።
ማንኛውም ዜጋ ወንጀል ሲፈጸም ወይም የወንጀል ጥርጣሬ ሲኖርበት በአካል ፖሊስ ጣቢያ መገኘት ሳያስፈልገው ካለበት ቦታ ሆኖ መረጃ እንዲሰጥ መተግበሪያው እንደሚያስችል በስልጠናው ተገልጿል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments