ባለስልጣኑ ከሲቪክ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሲቪክ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በከተማዋ የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡

ባለስልጣኑ ከሲቪክ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በከተማዋ የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ 24/3/2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከከተማው የሀይማኖት ተቋማት፣ ከወጣቶች ማህበራት ፣ ከአረጋውያን ማህበር ፣ከሴት ማህበር ፣ከነጋዴ ማህበር ፣ ከአካል ጉዳተኞች ማህበር እና ከእድር ምክር ቤት ተወካዮችና አመራሮች ጋር የደንብ መተላለፎች ለመከላከል በቅንጅት በሚሰሩ ስራዎች ላይ በመወያየት በቀጣይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ፡፡ የመድረኩን ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ ባለስልጣኑ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመዘርዘር ለአደረጃጀቶቹ ገለፃ አድርገዋል ፡፡ ዋና ስራ አስኪያጁ ከሴክተሮች ጋር በትስስር በመስራት ከፍተኛ ለውጥ መጣቱ ህዝብን ያሳተፈ ስራን ለመስራት ከሲቪክ ማህበራት ጋር ተቀናጅቶ መስራት የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ከተማ ለመፍጠር አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው ባለስልጣኑ ከሲቪክ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ያዘጋጀው መድረክ እና የትስስር ፕሮግራም ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ጠቁመው ባለስልጣኑ የከተማው ውብ፣ ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ባለስልጣኑ የሚሰራቸውን ስራዎች እና ሲቪክ ማህበራቱ በቅንጅት የሚሰሯቸውን ሰራዎች አስመልክቶ በዝርዝር በባለስልጣኑ በስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅትና አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀፀላ ቀርቧል፡፡ በዕለቱ በቀረበው የጋራ የቅንጅት አሰራር ዙርያ ከሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ በመሰጠት የስምምነት ፊርማ ስነ ሰርዓቱ በማከናወን መድረኩን ተጠናቋል፡፡

Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments