በአዲስ አበባ ልማት ስራዎች ሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንና ሴት ልጅ የአመራር ጥበብና በብልሃት የታየበት መሆኑ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ልማት ስራዎች ሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንና ሴት ልጅ የአመራር ጥበብና በብልሃት የታየበት መሆኑ ተገለጸ
30/06/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ማርች 8 “የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ'' በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት አከበረ ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሴቶች ሚና በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ መሆኑንና ሴት ልጅ ነገሮቹን በብልሃት ማለፍ የምትችል በየትኛውም የስራ ዘርፎች መሳተፍና ውጤታማ መሆን እንደምትችል እና ሴቶች ብዙ ጫና ቢኖርባቸውም ተቋቁመው ማለፍ እና ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ሴቶች የ50 ዓመታት የለውጥ ጉዞ እና የማርች 8 ታሪካዊ ፋይዳ የአዲስ አበባ ሁኔታ በሚል ቀኑን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ በባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ቀርቧል ።
ማርች 8 ሴቶችን በኢኮኖሚ በሞያና በጾታ በማደራጀት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚታሰብ ቀን ነው መሆኑ በሰነዱ ተገልጿል ።
የሴቶችን እኩልነት ማረጋገጥ የአንድ አካል ሳይሆን የሁሉም አካላት የጋራ ኃላፊነት ነው ያሉት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ወንዶችም የሴቶችን መብት በማስከበርና የሥራ ዕድል ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ አጋርነታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመራቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ሴቶች በከተማዋ "ስማርት ሲቲ" (Smart City) ግንባታ ላይ በልማት ስራዎች የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንና ሴት ልጅ የአመራር ጥበብና ብልሃት የታየበት መሆኑ ተመላክቷል።
በዝግጅቱ ላይ ልዩ ልዩ የሴቶችን ውጤታማነት የሴቶችን ብቃት፣ ጥንካሬ እና የኃላፊነት ብቃት የሚገልጹ ንግግሮችና ስነ- ፅሁፎች ቀርበዋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments