"ከተማችንን ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ለማድረ...

image description
- In code inforcement    0

"ከተማችንን ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን እናጠናክራለን” - ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ

"ከተማችንን ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን እናጠናክራለን” - ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ

              30/06/2018 ዓ.ም
                አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም የእውቅና እና የቀጣይ ወራት የተከለሰ ዕቅድ ውይይት መድረክ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት  ውጤታማ የሆኑ አፈፃፀሞች የተገኙት ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ ስራዎችን በዕቅድ መሠረት ማከናወን በመቻሉ በመሆኑ ያሉንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል አንዳንድ ክፍተቶችን በመሙላት በትጋት በትኩረት ቀንና ሌሊት በመሠራት ውጤታማ በመሆን ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

አክለውም ከተማችንን በፈጣን እድገት ላይ እንደመሆኗ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ማዘመን ለስራዎች መሳካት ጉልህ ሚና አለው ስለሆነው ሁሉም አካል እውቀቱን በየጊዜዉ ማጠናከር እንደሚያስፈልግና በግማሽ ዓመቱ ሳይከወኑ የቀሩና በክፍተት የታዩ ጉዳዮችን ዕቅድ በመከለስ የተሻለ ስራ ለማከናውን ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የቀጣይ ወራት የተከለሰ እቅድ እና የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ እውቅና ተሰጥቷል ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዓመት ማጠቃለያ ምዘና የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ክፍለ ከተሞች

1ኛ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ
2ኛ የንፋስ ስልክ ላፍቶ እና የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
3ኛ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ናቸው።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ ስድስት ወራት የከተማዋን ውበትና የመሰረተ ልማት ጥበቃ ስራው በዘላቂነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ  መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments