ባለስልጣኑ እየገነባቸው የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ስራዎች ከሚመለከታቸው የከተማው አመራሮች ጋር የደረሱበት ደረጃ ምልከታ አካሄደ
ባለስልጣኑ እየገነባቸው የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ስራዎች ከሚመለከታቸው የከተማው አመራሮች ጋር የደረሱበት ደረጃ ምልከታ አካሄደ
01/07/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተቋምን ለማዘመን እያለማቸው የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ስራዎች የባለስልጣኑ አመራሮች ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ምልከታና ግምገማ አካሄደ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ተቋሙ የአሰራር ስርዓቱን ዘመናዊ በማድረግ ከወረቀት ንክኪ የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስማርት ቢሮ (Smart Office) እየገነባ መሆኑን አስታውቋል ።
ተቋሙ የኮሪደር መሰረተ ልማቶችን ደህንነት ለመጠበቅና የወንዞችን ብክለት ለመቆጣጠር የዲጂታል መከታተያ ስልቶችን ስራ ላይ ለማዋል እየሰራቸው በሚገኙ በካሜራ ቴክኖሎጂ /ሲችዌሽን ሩም/ ለመደገፍ እና ስማርት የጥሪ መቀበያ ማዕከል መገንባቱ አስተዋውቋል።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ቀዳሚ ስራው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና በባህላዊ የወረቀት አሰራር ይፈጠሩ የነበሩ መስተጓጎሎችን ለማስቀረት የዲጂታል ቢሮ ግንባታውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አወል መሀመድ ደንብ ማስከበር በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን እና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት በዘመናዊ መንገድ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለመከላከል እያከናወነ ያለው ተግበርና እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ መሆን የሚችል መሆኑን ገልጸዋል ።
ስራዎችን በአስቸኳይ አጠናቆ ወደ ተግባር ለመግባት ተቋሙ ከፍተኛ ተነሳሽነት ያለው እንደመሆኑ አንዳንድ መስተካከል የሚገባቸውን ሶፍትዌሮችን የኛ ባለሙያዎች እዚህ ከአመራሩ ጋር በመግባባት ግልጽ የሆነ አሰራርን መከተል እንደሚገባና በቀጣይም በምንፈለገው መጠን በሙሉ አቅም እንደሚያግዙ የቢሮው ኃላፊ አቶ አወል ተናግረዋል ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍትዌር ፕሮግራም ባለሙያ አቶ ሀብታሙ ጴጥሮስ በቴክኖሎጂው ግንባታ የተከናወኑ ተግባራትና የባለስልጣኑ የጥሪ ማዕከል የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል።
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበርና በራሱ ባለሙያዎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን (ኔትወርክ) የመገንባት ስራዎችን በማከናወን አቅሙን እያሳደገ መሆኑን በሪፖርት ተገልጿል ።
ቀደም ሲል በከፍተኛ ወጪ በውጭ ድርጅቶች ይከናወኑ የነበሩ የኔትወርክ ዝርጋታዎችን፣ አሁን ላይ በቢሮው ባለሙያዎች (በሀገር ውስጥ አቅም) ለመስራት ጥረት በማድረግ ከፍተኛ ወጪን መቀነስ እንደተቻለ ተገልጿል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments