ባለስልጣኑ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በመበከል ጉዳት ያደረሰው ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፊል የስራ ክፍሎች ማሸጉን አስታወቀ
ባለስልጣኑ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በመበከል ጉዳት ያደረሰው ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፊል የስራ ክፍሎች ማሸጉን አስታወቀ
02/07/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻን በተደጋጋሚ ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ለብክለቱ መነሻ ችግሩ የሆኑ ክፍሎቹን በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
ድርጊቱ የተፈጸመዉ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ባንቢስ አከባቢ ሲሆን ተቋሙ ከአሁን በፊት የሽንትቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ በመልቀቅ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን 300 ሺህ ብር የቅጣት እርምጃ በመጀመሪያ በሁለተኛ ከቅጣፋቱ ሳይማር አሁንም በድጋሚ በመልቀቁ የቅጣቱን እጥፍ 600ሺህ የተቀጣ ቢሆንም አሁንም ድርጊቱን ለ3ኛ ጊዜ ባለማስተካከሉ የሆቴሉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ የመፀዳጃ ክፍሎቹን እንዲታሸግ ተደርጓል ።
ተቋሙ በቀጣይ በህግ ተጠያቂ በማድረግ ላደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በህጉ መሰረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተሰሩ ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማቶች በመበከል ለታለመለት አላማ እንዳይውል በሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሥልጣኑ አሳውቋል።
ተቋሙ ለከተማው ነዋሪዎችና ተቋማት በደንቡ ዙሪያ በተለያዩ አማራጮች ሰፊ ግንዛቤ መፍጠሩ አስታውሶ ነዋሪዎችና ተቋማት ከመሰል ተግባራቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments