ባለስልጣኑ " ጽዱ አከባቢ ለጤናማ ትውልድና ለተ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ " ጽዱ አከባቢ ለጤናማ ትውልድና ለተሟላ ስብዕና " በሚል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

ባለስልጣኑ " ጽዱ አከባቢ ለጤናማ ትውልድና ለተሟላ ስብዕና " በሚል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

                04/07/2018 ዓ.ም
                 አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ዙሪያ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአከባቢ ብክለቶችን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ላይ በትኩረት በመስራት  ህብረተሰቡ የደንብ ማስከበር አጋዥ ኃይል እንዲሆን በማድረግ የቆሻሻን አወጋገዳችንን በማዘመን የኮሪደር መሰረት ልማቶችንና የወንዝ ዳር ልማቶችን ለታሰበላቸው አላማ ብቻ በመጠቀም ብክለትን በዘላቂነት መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከተማችን ላይ የሚታዩትን ብክለቶች ለመከላከል በፌደራል ደረጃ የወጣውን አዋጅ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ኖሮት የወጡትን  ህጎችን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ገልጸዋል ።

አክለውም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው በቀጣይም በሰፊው እንደሚሰራና ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጋር የጀመረዉ ቅንጅታዊ ስራዎች አጠናክሮ በመቀጠል ከተማችን ውብ ጽዱ ለነዋሪዎቿና ለእንግዷቿ ምቹ እንድትሆን በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የድምፅ ፣ የፍሳሽና የፕላስቲክ ብክለት አከባቢያዊ ችግሮች ላይ ደንብ ማስከበር ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የግንዛቤ ስልጠና ሰነድ በአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአከባቢ ብክለት ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መላቱ ወሰኑ ቀርቧል ።

በሰነዱ የፕላስቲክ ብክለት በአዲስ አበባ፣ የፕላስቲክ የድምፅና የፍሳሽ ብክለት አይነቶች እና አዋጅ ቁጥር 1383/2017 በሰፊው ተዳሰዋል ።

ማንኛውም የህብረተሰብ አካል ከመኖሪያ ቤት ይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ ሀያ ሜትር ፤ የአገልግሎት መስጫ እና የንግድ ተቋማት እስከ ሀምሳ ሜትር ደረቅ ቆሻሻን የማጽዳት ኃላፊነት ተጥሎበታል ።

አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረቲጥት የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ከሁለት ሺህ ብር በማያንስና ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጯ እንደሚቀጣ በሰነዱ ተገልጿል ።

የፕላስቲክ ብክለት የከተማ ገፅታን የሚያበላሽ፣ በመንገዶችና በሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርስ እና አፈርን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚበክል እንዲሁም የጎርፍ ማስወገጃ ቱቦዎችን በመድፈን የጎርፍ አደጋን ሊያስከትል እንደሚችልና ፕላስቲኮች ሲቃጠሉ የሚለቀቀዉ መርዛማ ኬሚካል የአየር ብክለትን ሚያስከትል መሆኑም ተመላክቷል፡፡  

በተጨማሪም ስነምግባርና ብልሹ አሰራርን ለመከለል የህብረተሰቡ ሚና በሚል የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ባለስልጣኑ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ቀርቧል።

ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን በዘለቄታው ለመቅረፍ የህግ እርምጃ ብቻ እንዳልሆነና የማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና መዳበር መሰራታዊ መፍትሔ እንደሆነ ተገልጿል ።

ህብረተሰቡ ሌብነት ፣ ብልሹ አሰራርና የስነምግባር ችግሮችን ለመከላከል እንዲችልና የበኩሉን እንዲወጣ ለማስቻል ስልጠናው ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አቶ እዮብ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውየይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments