ባለስልጣኑ የግንዛቤ ስራዎች በማጠናከር የእርምጃ አወሳሰድ ስራዎች ለመቀነስ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ባለስልጣኑ የግንዛቤ ስራዎች በማጠናከር የእርምጃ አወሳሰድ ስራዎች ለመቀነስ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
07/07/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየካቲት ወር የደንብ መተላለፎች የመከላከል ፣የመቆጣጠር እና አስተዳደራዊ እርምጃ ስራዎች በተመለከተ ከክፍለ ከተማና ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ግምገማዊ ውይይት አካሄደ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተሻለ አፈጻጸም በታየባቸው የደንብ ጥሰቶች ላይ በማጠናከር ክፍተት የታየባቸው አፈፃፀም ላይ ወቅቱን መሠረት ያደረገ ትኩረት በማድረግ ተቋሙ የያዘውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።
በመድረኩ በየካቲት ወር እቅድ በዘጠኙ ዋና ዋና የደንብ መተላለፎች የመከላከል ፣የመቆጣጠር እና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ስራዎች በድክመት፣ በጥንካሬና ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየካቲት ወር የተከናወኑ አበይት ተግባራት ፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች ፣ የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት መስኮች የተመለከተውን ሪፖርት ቀርቧል።
በተጨማሪም በመድረኩ በንብረት አያያዝ አወጋገድ እና አሻሻጥ ላይ የተደረገ የጥናት ሰነድ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ቀርቧል ።
በክፍለ-ከተማ እና በወረዳ የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤቶች በኩል የሚወረሱ ንብረቶች ለጨረታ ቀርበው ለመንግስት ገቢ እስከሚሆኑ ድረስ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ መጋዘኖችን ማዘጋጀትና የተያዙ ንብረቶች ሳይበላሹ ወይም ሳይጠፉ በተገቢው ሁኔታ እንዲቀመጡ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል ።
ጥናቱ በዋናነት የአሰራር ግልጽነትን፣ የባለሙያዎችን ታማኝነት እና የተወረሱ ንብረቶች በአግባቡ ተሽጠው መልሰው ለከተማው ልማት የሚውሉበት አሰራር ማጠናከር እንዳለበት ተመክራል።
በመጨረሻም ለስራው መሳካት በተነሱ ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዶ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ የግንዛቤ ስራዎች በማጠናከር የእርምጃ አወሳሰድ ስራዎች ለመቀነስ መሰራት እንዳለበት ገልፀው የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል ።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments