ለከተማችን አዲስ አበባ እድገትና ምሳሌነትዋ የ...

image description
- In code inforcement    0

ለከተማችን አዲስ አበባ እድገትና ምሳሌነትዋ የሚያስቀጥል አመራርና ሰራተኛ እየተገነባ ነው።"ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ

"ለከተማችን አዲስ አበባ እድገትና ምሳሌነትዋ  የሚያስቀጥል አመራርና ሰራተኛ እየተገነባ ነው።"ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
                
              16/07/2018ዓ.ም
                  **ሰንዳፍ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በማዕከል ፣ በክፍለከተማና ወረዳ ለሚገኙ አመራሮች ሰንዳፍ በሚገኘው የኢትዮጲያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ የአካል ብቃት እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን ለመስጠት በዛሬው እለት የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እዲሁም የዮኒቨርስቲው አመራሮች በተገኙበት የመክፈቻ ፕሮግራም አካሄደ።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስልጠና ክፍል ምክትል ፕሬዝዳንት  ረዳት ኮምሽነር ደረጀ አስፋው  ወደ ሁለተኛ ቤታችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የራሳችን ተልእኮ ቢኖረንም ግባችን ግን አንድ ስለሆነ አዲስ አበባ ከተማ እያደገችና እየተለወጠች በመሆኑ ይህን እድገትና ለውጥ የሚያስቀጥል አመራር ስለሚያስፈልግ ስልጠናው ወቅቱን የዋጀ ነው ብለዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ያሉንን ጥንካሬዎችና ያሉብንን ክፍተቶች በመገምገም ብሎም ከማህበረሰቡ በተለያየ ጊዜ በተሠጡን ሀሳብ አስተያየት መሰረት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚያስፈልግ በማመን ይህ ስልጠና ተዘጋጅቷል::

ስልጠናው የተቋሙን ተልእኮ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማላቅ ፤ የከተማችን አዲስ አበባ እድገት በሚመጥን መልኩ አገልግሎት ለመሠስጠት የሚያስችል የአመራር ቁመና ለመላበስ ና ተልእኮዎቻችንን በምናስፈጽምበት ጊዜ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የአገልግሎት እርካታን ለማረጋገጥ የሚያስችለንን አቅምን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ሰልጠና ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የተቋም ግንባታ ስራችንን እያጠናቀቅን በመሆኑ ከዚህ በኋላ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየሰራን እንገኛለን ለሰራተኞችና ተገልጋዬች ምቹ የስራ አካባቢን ፈጥረናል በተለያዮ መንገዶች የተቋም ግንባታችንን እያስቀጠልን እንገኛለን ብለዋል።

በመጨረሻም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል የስልጠናውን ግብ ለማሳካት እንደሰልጣኝ የሚጠበቅብንን ድርሻ እንድንወጣ አደራ ማለት እፈልጋለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments