ባለስልጣኑ ለአዳማ ከተማ የሰላምና ጸጥታ ልዑካን ቡድን የልምድ ልውውጥ አደረገ
ባለስልጣኑ ለአዳማ ከተማ የሰላምና ጸጥታ ልዑካን ቡድን የልምድ ልውውጥ አደረገ
መጋቢት 17/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታና የደንብ ማስከበር የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋማዊ አደረጃጀትና አሰራር ዙሪያ የልምድና ተሞክሮውን አጋራ።
በልምድ ልውውጥ መድረኩ መክፈቻ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አዲስ አበባ በተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እያጌጠችና እድገቷ እየተፋጠነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ከተማ አስተዳደሩ ያወጣቸውን ደንቦችና አዋጆች የማስከበር ኃላፊነት የባለስልጣኑ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከላከል፣ በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ ረገድ እያከናወነ ያለውን ስራ በማብራራትም መድረኩን አስጀምረዋል።
የልምድ ልውውጡ "የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከየት ወደ የት?" በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን፣ በተቋሙ አመሰራረት፣ አወቃቀር እና በ9ኙ የደንብ ጥሰቶች ላይ የሚከናወኑ የመከላከል፣ በመቆጣጠርና የእርምጃ አወሳሰድ ሂደቶች የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ላይ ተሰጥቷል።
የልምድ ልውውጡ የተቋማዊ ግንባታንና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን የሚያሳይ መረጃ በሰነድ በባለስልጣኑ የቀረበ ሲሆን ።
የልዑካን ቡድኑ አባላትም የተቋሙን አሁናዊ ቁመናና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚያሳዩ የቢሮና የስራ ክፍሎች ምልከታ አድርገዋል።
በዚህም የቴክኖሎጂ ነክ ስልጠና መስጫ ክፍሎችን፣ የኮንፈረንስ አዳራሾችን እና ዘመናዊ የጥቆማ መቀበያ ክፍሎችን ጨምሮ ሌሎች የስራ ክፍሎችን በባለስልጣኑ አመራሮች አማካኝነት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የልዑካን ቡድን አባላቶች ወደ ተቋም ግንባታ ለመሻገር የሚያስችሉ ሰፊ እውቀቶችና ተሞክሮ ማግኘታቸውን በመጥቀስ፣ የተገኘውን ልምድ በከተማቸው ተግባራዊ ለማድረግ መነሳሳታቸውን አረጋግጠዋል።
በልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሩም የተመረጡ በክፍለ ከተሞች፣የከተማው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እና የወረዳ ጽ/ቤት የመስክ ምልከታ ተደርጓል።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments