ተቋማት የሳይበር ሴኩሪቲ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ...

image description
- In code inforcement    0

ተቋማት የሳይበር ሴኩሪቲ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ከዘመኑ ጋር እኩል መራመድ እንደ ሚያስፈልግ ተገለፀ

ተቋማት የሳይበር ሴኩሪቲ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ከዘመኑ ጋር እኩል መራመድ እንደ ሚያስፈልግ ተገለፀ

          መጋቢት 23 2018 ዓ ም
           ** ሰንዳፋ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስትራቴጂክ አመራሮች በሳይበር ሴኩሪታ እና በዲጅታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም  ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባለስልጣኑ  የደንብ መተላለፎችን  ውጤታማ በመሆነ መልኩ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር   የቴክኖሎጂ አገልግሎት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ አመላክተዋል።

ስልጠናው የሰጡት ዋና ኢንፔክር መሠረት አበበ የሳይበር ጥቃት ዘመኑን ያመጣውና የተቋማትና የግለሰብ የቴክኖሎጂ አገልግሎት ፈታን እያደረገው መሆኑ ገልፀው ለዲጅታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደህንነት ሁሉም ተቋማትና ግለሰብ ማስጠበቅ ካልቻሉ ህይወታቸው አደጋ ውስጥ እንደሚወድክ አስረድተዋል።

በዕለቱ ተግባቦት ማጠናከር አገልግሎት ቀላልና ውጤታማ በማድረግ የአመራርነት ስኬትን መጎናጸፍ እንዲሁም በማህረሰብ ዘንድ በጎ ተጽኖን  መፍጠር እንደሚቻል የኢ/ያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  ኢ/ር ፍፁም ብርሀኑ  በሰጡት ስልጠና ገልጸዋል።

በእለቱ የኮሙኒኬሽን፣የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ሳይንሳዊ አሰራር እና አጠቃቀም ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።

ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments