"ኦፊሰሮች ደንብ ሲስከብሩ ህግንና መመሪያን ጠንቅቆ ማወቅና የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ሊወጡ ይገባል" ረ/ፕ ኤርሚያስ ከበደ ዶ/ር
"ኦፊሰሮች ደንብ ሲስከብሩ ህግንና መመሪያን ጠንቅቆ ማወቅና የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ሊወጡ ይገባል" ረ/ፕ ኤርሚያስ ከበደ ዶ/ር
26/07/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልደታ ክ/ከተማ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር መመሪያዎችና በአገልግሎት አሰጣጥ ስነ-ምግባር ላይ ስልጠና ተሰጠ።
የክፍለ ከተማውና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተሰጠው ስልጠና በዋናነት ኦፊሰሩን በሞያዊ ስነ-ምግባር በማነጽ ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግልበትን መንፈስ ለመገንባትና የከተማ አስተዳደሩ የሚያወጣቸውን አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ኦፊሰሩ በሚገባ ተረድቶ ተግባራዊ እንዲያደርግ ለማስገንዘብ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ስልጠናው በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ መምሪያ ኃላፊ ዋ/ኢር ዶ/ር ኤርሚያስ ከበደ በስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 03/2015 እና ደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ. መሰረት በማድረግ በየአገልግሎት አሰጣጥና በሙያዊ ስነ-ምግባር ላይ ተሰጥቷል።
ዋ/ኢር ዶ/ር ኤርሚያስ በመድረኩ ላይ እንዳብራሩት፤ የደንብ ማስከበር ስራ ውጤታማ እንዲሆን ኦፊሰሩ ህዝብን አክባሪ፣ ሚስጥር ጠባቂ፣ታማኝ፣ታጋሽ እና ብልሹ አሰራርን በመጸየፍ ህብረተሰቡ ሲያገለግልና የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ሲወጣ ተቋሙ የህዝብ ተቀባይነት ያገኛል ብለዋል።
በስልጠናው እያንዳንዱ ኦፊሰር የተቋሙ አምባሳደር መሆኑን ተረድቶ፣ ራሱን በመልካም የሞያ ስነ-ምግባር በማነጽ ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለበትም በጥልቀት ተመላክቷል። ይህም በተቋም ግንባታና በህዝብ አመኔታ ላይ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች እንዲህ ያሉ አቅምን የሚገነቡ ስልጠናዎች ህግንና መመሪያን ጠንቅቆ ለማወቅና በመሬት ላይ ያሉ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ለመወጣት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
ኦፊሰሮቹ አክለውም በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በመጠቀም ህዝብን በታማኝነት በማገልገልና ብልሹ አሰራሮችን በጽናት በመታገል የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት ቃል ገብተዋል።
ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments