በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ82%...

image description
- In code inforcement    0

በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ82% መቀነሱ ተገለፀ ።

በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ82% መቀነሱ ተገለፀ ።

             08/08/2018 ዓ.ም
               **አዲስ አበባ**   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት  በከተማዋ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ እና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወኑ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 82% መቀነሱን ገለፀ ።

ተቋሙ ሥራውን በቴክኖሎጂ ለማገዝ የኮል ሴንተር (Call Center) እና ስማርት አይሲቲ (Smart ICT) የሥልጠና ክፍሎችን ገንብቶ ወደ ሥራ አስገብቷል ፣ቅሬታዎችን በፍጥነት ለመፍታትና የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ ዲጂታል አሠራሮች ተዘርግተዋል እንዲሁም ሠራተኞችን የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሥነ-ምግባር ለማሻሻል የሚያስችሉ የለውጥ ሥራዎች ማከናወኑ አስታውቋል።

ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እና አመራሮች የንድፈ ሐሳብና የተግባር ስልጠናዎችን በመስጠት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሥነ-ምግባር እና በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ለውጥ መምጣቱ ተገልጿል ።

በቀጣይ ባለስልጣኑ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራውን በማጠናከርና የህብረተሰቡን ተሳታፊነት በመጨመር የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በማረም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ማራኪና ሰላማዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ  አስታውቋል። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments