
ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።
ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።
30/03 /2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግርና የቁርስ ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት አካሄደ፡፡
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት በሳምንቱ ያሉትን የስራ ጊዜያቶች በንቃት ለማሳለፍና
በአመራሩና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቀራርቦ ለመስራት ፕሮግራሙ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሐመድ የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮና ልምዳቸውን አጋርተዋል።
በመድረኩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ካሳሁን ስለ ተቋሙ ድህረገጽ (Website) አጠቃቀም እንዲሁም ጠቀሜታውን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments