የደንብ መተላለፎች በመከላከል የከተማዋን ገጽታና የገነባው የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በቢሮ ሪፎርም ስራዎቹ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ
የደንብ መተላለፎች በመከላከል የከተማዋን ገጽታና የገነባው የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በቢሮ ሪፎርም ስራዎቹ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ
21/08/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ባለፉት ሦስት ዓመታት ያከናወናቸውን የተቀናጁ የሪፎርም ስራዎች ዛሬ ጠዋት በዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት የጎበኙ ሲሆን ተቋሙ ከዚህ ቀደም ይነሳበት የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል መሰረታዊ ለውጥ ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ነዋሪዎች ቀደም ሲል ለተቋሙ ሰጥተውት የነበረውን አላስፈላጊ ስም ለመቀየር በአስተሳሰብ፣ በሥነ-ምግባር እና በዘመናዊ አሰራር ላይ ተከታታይ ስራዎች ተከናውነዋል።
በዚህም ተቋሙን ከወረቀት ንክኪ ነፃ በማድረግ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማለትም በተለያዩ የስራ ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጥ የጥሪ ማዕከል፣ የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል፣ የስማርት ስልጠና ማዕከል እና ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀቶች ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ተመልክተዋል።
ለህዝብ ግንኙነት ስራዎች ተብሎ የተገነባው የድምፅና ምስል ስቱዲዮ ደግሞ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ለህብረተሰቡ በስፋት እንዲደርስ እያገዘ ይገኛል፡:
ከቴክኖሎጂ ሽግግሩ ጎን ለጎንም ባለሥልጣኑ ለሰው ኃይል በሰጠው ልዩ ትኩረት ለሰራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ያስቻሉ የህፃናት ማቆያ፣ የሰራተኛ ካፌቴሪያ፣ የሸማቾች ሱቅ እና የሰውነት ማጎልመሻ ማዕከልን በማደራጀት ወደ ስራ አስገብቷል።
እነዚህ የተቀናጁ የሪፎርም ስራዎች በውጤት ታጅበው በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉ ተገልጿል ።
በመጨረሻም ክብርት ከንቲባዋ ለተመዘገበው ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የተቋሙን አመራሮችና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮን አመስግነዋል ።
ባለስልጣኑ ያገኘውን የለውጥ ተሞክሮ እስከ ታችኛው የክፍለ ከተማና የወረዳ መዋቅር ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments