በበጀት አመቱ ባለፉት 9 ወራት የደንብ መተላለፎች በ82% እና የወንጀል ምጣኔ በ47% መቀነስ መቻሉ ተገለፀ
በበጀት አመቱ ባለፉት 9 ወራት የደንብ መተላለፎች በ82% እና የወንጀል ምጣኔ በ47% መቀነስ መቻሉ ተገለፀ
22/08/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከተማችን የአፍሪካ ትልቋ የቱሪዝም የስህበት ከተማ ሆናለች፤ የከተማዋ ሰላምና ደህንነት አስተማማኝና በመሆኑ በርካታ ሀገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ሁነቶች እየተካሄዱባት ይገኛል፤ ይህንንም ማድረግ የቻልነው ህዝቡን በቀጥታ የሰላም ባለቤት ማድረግ በመቻሉ መሆኑ ገልፀዋል።
በከተማው ከ200ሺ በላይ ለሚሆኑ የሰላም ሰራዊት አባላት በ9 ወራት ውስጥ በድግግሞሽ የአቅም ግንባታ ስራዎች መሰራታቸውን በከተማችን የደንብ መተላለፎች እንዲቀንሱ እና ለከተማዋ የሚመጥን ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ለማፍራት ወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን በመስጠት የሰው ኃይሉ ላይ ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ተናግረዋል።
በዕለቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በባለፍት 9ወራት የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ እና የተለያዮ የደንብ መተላለፎች እንዳይከሰቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው።
ይህንንም ለማሳካት ቀደም ብለን ስራዎችን በእቅድ አዘጋጅተን በየሩብ ዓመቱ መገምገም መቻሉን ተናግረው። በዛሬው ዕለትም ምን ሰራን የሚለውን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ተቀብለን የምንወጣበት መሆኑን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት በከተማዋ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ እና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወኑ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 82% መቀነሱን ሪፖርቱን ያቀረቡት የባስልጣኑ የእቅድ እና በጀት ዳይሬክተር ኮነሬል አድማሱ ተክሌ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንዳሉት በ9ወራት የወንጀል ምጣኔ ከቀደሙት ጊዜያት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ 47.15 በመቶ መቀነሱን ገልፀዋል።
በመጨረሻም ለመድረክ የቀረቡትን ሀሳብ እና አስተያየቶች ላይ ምላሽ በሁለቱ ተቋማት አመራሮች ምላሽ ተሰቶበት እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ኮሙኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments