በማዕከል የተጀመረውን የሪፎርም ጉዞ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የቦሌ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ገለጸ
በማዕከል የተጀመረውን የሪፎርም ጉዞ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የቦሌ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ገለጸ
24/08/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የቦሌ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በከተማ እናት መስሪያቤቱ የተጀመረው የሪፎርም፣ የተቋም ግንባታ እና ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ተግባር አጠናክሮ ለማስቀጠል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀመጠ ::
ጽ/ቤቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ያስቀመጠው በክፍለ ከተማው ተቋም በመምራት የላቀ አስተዎጽኦ ላበረከቱ የቀድሞ አመራሮች እውቅና ምስጋና በሰጠበት መድረክ ሲሆን ይህም በቀጣይ ተግተው ለሚሰሩ አመራሮች እና ኦፊሰሮች የበለጠ የሚያበረታታ መሆኑ የቦሌ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቸሩ ጌታቸው ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተቋም ግንባታ ስራ በማከናወን ከህብረተሰብ የሚነሳውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ተግባሩ ወደ ዲጂታል መቀየሩ ገልፀዋል።
ደንብ ማስከበር የቀድሞ ስሙን በመቀየር አሁን ላይ ራሱን በማዘመን የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት በመፈጸምና በኃላፊነት በመወጣት እና የአደባባይ ፕሮግራሞች እና በአደባባይ የሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የቦሌ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈጸሚ ወ/ሮ አንቺነሽ ተስፋዬ ተናግረዋል።
ምክትል ስራ አስፈጸሚዋ የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በማዕከል ተቋሙ የተጀመረው የሪፎርምና የተቋም ግንባታስራ ለማስቀጠል ክፍለ ከተማው በሙሉ አቅሙ ለማገዝና ለማስተግበር ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም በክፍለ ከተማው በአመራርነት ያገለገሉ የቀድም የክፍለ ከተማ ሀላፊው ኮ/ር አሰፋው የሺዳኜ እና ሌሎች የወረዳ አመራሮቹ በክብር ሸኝቷል።
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments