ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን በሰላም እንዲጠናቀቅ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑ ተገለፀ
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን በሰላም እንዲጠናቀቅ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑ ተገለፀ
12/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቅድመ ምርጫ በምርጫ እለት እና በድህረ ምርጫ ወቅት የተቀናጀና የተጠናከረ የጥበቃና የሰላም ግንባታ ተግባራትን በማከናወን ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናወን የውይይት መድረክ አካሄደ ።
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ እጅግ ሰላማዊ ፣ ነጻ ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒ በማድረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል ።
አክለውም የደንብ ማስከበር አመራርና ኦፊሰር ምርጫው በከተማችን በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙ ሲሆን ይሄንንም በቀጣይ በምርጫ እለት እና በድህረ ምርጫ ወቅት አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ለሀገራችን ሰላም እና ደህንነት በጋራ መቆም እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል ።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments