በህብረተሰቡ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ።
በህብረተሰቡ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ።
13/09/2018 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 150/2015 ለማስፈጸም በወጣ የአፈጻጸም መመሪያ 2/2015 ላይ ለከተማው ነዋሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አሰኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከህብረተሰቡ የሚሰጡ ግብዓቶችን ወደ ተቋሙ እቅድ በማካተት ስራዎች በጋራ መሰራታቸውን በመግለጽ በቀጣይም ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጋር ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
አክለውም ተቋሙ በተለያዩ ወቅቶች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በስፋት በመስራት ከመቅጣት በፊት አስቀድሞ የደንብ መተላለፎች የመከላከል ስራን በማከናወን በከተማችንን የደንብ መተላለፍ እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ።
ባለስልጣኑ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድ ሰው ተኮር ሰራዎችን በማከናወን ወላጆቻቸው ያጡ ህጻናትን መንከባከብና መደገፍ እንዲሁም አስራ ሰባት የአቅመ ደካማ ቤት በተለያዩ ክ/ከተማዎች ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ ማስረከቡ ተገልጿል ።
በመድረኩ ተቋሙ ሪፎርም በማድረግ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባለስልጣኑ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
በመጨረሻም ከመድረኩ ተሳታፊ ህብረተሰብ ውይይት በማድረግ የተቋሙ የሪፎርም ስራዎች በማስጎብኘት ህብረተሰቡ ተቋሙን በማገዝ የደንብ መተላለፎች በከተማው እንዲቀንስ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠይቋል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments