
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ እና በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ እና በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።
30/03/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሜንስትርሚንግ ቡድን ከአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ37ተኛ በሀገራችን ለ36ተኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን በተመለከተ እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ዙሪይ ግንዛቤ ተፈጠረ።
በመድረኩ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ እንደተናገሩት ቀኑ በዋነኝነት የሚከበረው በበሽታው አማካኝነት ሂወታቸውን ላጡ አካላት መታሰቢያና በቀጣይ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመግታት ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። በመሆኑም ራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን ከዚህ አስከፊ በሽታ መጠበቅ ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።
የዓለም ኤች አይቪ ኤድስ ቀንን በተመለከተ የውይይት ሰነድ እና ስለ ማህጸን ጫፍ በር ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የኤች.አይ.ቪ ሜንስትርሚንግ ቡድን መሪ በሆኑት አቶ ወንድሙ ደንቡ ቀርቧል።
በሰነዶቹም ኤች.አይ.ቢ ኤድስ ዛሬም ለሀገሪቱ ስጋት እንደሆነና ሁሉም አካል የቫይረሱን ስርጪት ለመግታት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር አሁን ላይ በሀገሪቱ በስፋት እየተስተዋለ የሚገኝና በገዳይነቱም በስፋት ከሚታወቁት የካንሰር አይነቶች ተርታ የሚመደብ በመሆኑ አስቀድሞ በመመርመር፣ ከጋብቻ በፊት በመታቀብ እዲሁም በመወሰን በሽታውን መከላከል እንደሚገባ በውይይት ተብራርቷል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments