ኮሪደር መሰረተልማቶች እንዲጠበቁ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለ ስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ
"ባለስልጣኑ በምሽት የንግድ እንቅስቃሴው እንዲሳለጡ እና የኮሪደር መሰረተልማቶች እንዲጠበቁ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለ ስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ
14/09/2018 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሶስተኛ ሽፍት የምሽት የደንብ ማስከበር አገልግሎት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ መሪነት በአራዳ፣ በቂርቆስና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የባለስልጣኑ ኮሙኔኬሽን እና የሚዲያ አካላት ተዘዋውረው ባደረጉት ምልከታ የመስክ ኦፊሰሮቹ አስቀድመው ቦታቸውን በመያዝ የደንብ መተላለፎችን ሲከላከሉ፣ግንዛቤ ሲፈጥሩ እና የኮሪደር መሰረተ ልማቶች ጥበቃ ሲያደርጉ ተመልክቷል።
የምሽት ሽፍት ህብረተሰቡ ወደየቤቱ የሚገባበት በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ፍሰት የሚስተዋልበትና የደንብ መተላለፍ ተግባራት በስፋት የሚታይበት ፈረቃ በመሆኑ በተለይም ዋና መንገዶችን ለተገልጋይ ነፃ የማድረግና የትራንስፓርት ፍሰቱን የማሳለጥ ስራ ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የቅኝት ቡድኑ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
የኮሪደር ልማቱ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዘረጋው ዘመናዊ አሰራር መሠረት ከዚህ ቀደምት በምሽት ክፍለ ጊዜው የሚታየው የደንብ መተላለፍ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ከአከባቢው ነዋሪዎችን እና ከነጋዴዎች ገልፀዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራም በስፍራው በተዘዋወርንበት ወቅት አግኝተን እንዳናገርናቸው፤ ተቋሙ በከፍተኛ ለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሚገኝና ከዘጠኙ የደንብ መተላለፍ ተግባራቶች በተጓዳኝ በ7/24 የፀጥታ ስራውም ላይ አጋዥ በመሆን ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝና ህብረተሰቡም ለተቋሙ የሚሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።
ማህበረሰቡ ያለ ስጋት በተገነቡ ፓርኮች እንዲዝናና ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፍ የተገነቡት ፓርኮችም ንፅህናቸውና አረንጓዴ ስፍራነታቸው ተጠብቀው እንዲቆዩ ኦፊሰሩ በትኩረት እየጠበቀ እንደሚገኝም ገልፀው ፤ባለስልጣኑ በምሽት የንግድ እንቅስቃሴው እንዲሳለጡ እና የኮሪደር መሰረተልማቶች እንዲጠበቁ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።
የመስክ ኦፊሰሮቹም የምሽት ስራ ፈታኝና አስቸጋሪ ቢሆንም በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት በቁርጠኝነት ተልዕኮዎቻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ የመስክ ክትትል፣ ቁጥጥርና ግንዛቤ ስራውን በሶስት ሽፍት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 4 ሰዓት ድረስ እንደሚሠራ ይታወሳል።
ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments