ባለስልጣኑ በቀጣይ አምስት ዓመት የደንብ መተላለ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በቀጣይ አምስት ዓመት የደንብ መተላለፎች የቁጥጥር ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመተግበር እንደሚሰራ ገለፀ

ባለስልጣኑ በቀጣይ አምስት ዓመት የደንብ መተላለፎች የቁጥጥር ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመተግበር እንደሚሰራ ገለፀ

      ግንቦት 28 2018 ዓ.ም 
     **** አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2022 ዓ ም ራዕዩንና ለማሳካትና ስማርት ሲቲ ለመፍጠር የተጀመረውን ጉዞ እውን ሊያደርግ የሚያስችል የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ። 

በውይይቱ ተቋሙን በቴክኖሎጂ በማላቅ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ በ2022 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማን ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት እንድትሆን ባለስልጣኑ ያስቀመጠውን ራዕይ እውን የሚያደርግ ነው ሲሉ የባለስልጣኑ  ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ አምስት አመት የደንብ መተላለፎች የቁጥጥርና ሂደቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተግበር በከተማ የሚስተዋሉ ደንብ መተላለፎችን በመቀነስ ለነዋሪዎቿ እንዲሁ ለእንግዶቿ ምቹና ሰላማዊ የሆነች አዲስ አበባን ለመረጋገጥ መሆኑ በእቅዱ ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በማዕከል የተጀመረው የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በማላቅ እስከ ታችኛው መዋቅር  ተደራሽ በማድረግ የተቋሙን ራዕይና ተልእኮ  ባለ ድርሻ አካላትና ህብተሰቡ የሚሳተፉበት ስልት መነደፉን በውይይቱ ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ ውጤት ተኮር ስራዎችን በማከናወን የተገልጋይ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ አገልግሎት አሰጣጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ  ተገልጿል። 

መረጃው:- የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments