የከተማችን ስነ-ምህዳር ጤንነት በማስጠበቅ የደን...

image description
- In code inforcement    0

የከተማችን ስነ-ምህዳር ጤንነት በማስጠበቅ የደንብ መተላለፎች ለመከላከል ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

የከተማችን ስነ-ምህዳር ጤንነት በማስጠበቅ የደንብ መተላለፎች ለመከላከል ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ 

              06/10/2018 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በደንብ 180/2017 ወንዝና  የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ብክለት መከላከልና በአዋጅ ቁጥር  1383/2017 ስራዎች ዙሪያ በተመለከተ የውይይት መድረክ ተካሄደ ። 

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እሸቱ ለማ ከተማችንን ንጹህ ውብ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለቱሪስት መስብ የአፍሪካ ተምሳሌት እንድትሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በመስራትና የግንዛቤ ስራዎች በስፈት በመከናወኑ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል። 

የፕላስቲክ ምርቶች /ፌስታሎች / በተፈጥሮ ለረጅም ጊዜ ሳይበሰብሱ የሚቆዩ በመሆናቸው የአከባቢ ስነምህዳር ብሎም የሰዎች እና የእንስሳት የጤና ጠንቅ በመሆናቸው ህብረተሰቡ እነዚህን የጤና ጠንቅ የሆኑ ምርቶችን ባለመጠቀም አጠቃላይ የስነምህዳር ጤንነትን በማስጠበቅ ሂደት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ዶ/ር እሸቱ ገልጸዋል ። 

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ወንዞችን እና የወንዙ ዳርቻዎችን ከብክለት ጽዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በጋራ በመቀናጀት ለመከላከልና የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በርካታ ተግባራትን በጋራ በማከናወን አመርቂ ስራ መሰራቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል ። 

አክለውም ከቅጣትና ከደንብ ማስከበር ባለፈ፣ ህብረተሰቡ ስለ አካባቢ ጥበቃና ስለ ቆሻሻ ጉዳት በቂ ግንዛቤ አግኝቶ ቆሻሻን የሚፀየፍ ትውልድ እንዲፈጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባና ህግንና ደንብን ተላልፈው አካባቢን በሚበክሉ አካላት ላይ ጥብቅ የደንብ ማስከበር ስራ እንደሚሰራና  ተጠያቂነት እንደሚሰፍን አስገንዝበዋል። 

በመድረኩ በደንብ 180/2017 የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል በአዋጅ ቁጥር 1383/2017 በጋራ የተሰሩ ጥቅል ስራዎች ሪፖርት እና የፕላስቲክ ከረጢት አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የህግ ተከባሪነት የመስክ ሪፖርት ቀርቧ ውይይት ተካሂዷል ። 

በአዋጅ 1383/2017 የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ላይ የፕላስቲክ ብክለትን ለመቀነስ አዋጁን ለመተግበር  በተደረጉ የቅጣት እርምጃዎች ህግን ባለመክበር 60 አካላት በድምሩ 1.3 ሚሊዮን ብር መቀጣታቸው በሰዱ ተገልጿል ። 

ከተማችን ከአካባቢ ብክለትና ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለማድረግ  ከላይ አስከ ታች ያለው መዋቅር በቅንጅትና በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል 

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments