ባለስልጣኑ አዲስ የፓራ-ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ትውውቅ አደረ
ባለስልጣኑ አዲስ የፓራ-ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ትውውቅ አደረገ
13/10/2018 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ተቋሙ እየገነባው ካለው ዘመናዊ አደረጃጀትና ሙያዊ ስነምግባር የሚመጥን አዲስ የደንብ ልብስ በዛሬው ዕለት በይፋ ለህብረተሰቡ አስተዋውቋል።
የተዘጋጀው አዲስ የደንብ ልብስ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና ደረጃዎችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን አባላቱም ይህንን አዲስ የደንብ ልብስ ሲለብሱ ትልቅ ህዝባዊ አደራ መሸከማቸውን ተገንዝበው በኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚገባቸው ተገልጿል።
የደንብ ማስከበር አባላት ከዚህ በፊት ሲለብሱት ከነበረው የደንብ ልብስ በተጨማሪ በዛሬው የተዋወቀው የደንብ ልብስ የለበሱ አባላት መሆናቸውን ተረድቶ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ባለስልጣኑ አስታውቋል።
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
ጠንካራ የአገልግሎት ስርዓት ያላቸው ፣ ስነምግባር የተላበሱ ፣ አገልጋይ ባለሙያዎችን እና አመራሮችን የመፍጠር ተቋማዊ የሪፎርም ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments