ባለስልጣኑ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር የሚዲያ ስራዎች የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ
ባለስልጣኑ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር የሚዲያ ስራዎች የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ
16/10/2018 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሚያከናውናቸውን ተግባራት ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽነቱን ለማስፋት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በ2019 በጀት ዓመት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተፈራርመዋል ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተቋማቸው ራዕይ ለማሳካትና የተቋሙ መረጃዎች ወደ ሰፊው ማህበረሰብ ለማስፋት ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር የስራ ስምምነት መፈራረም ማስፈለጉን አብራርተዋል፡፡
ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር እየተሰሩ የሚገኙት ፕሮግራሞች ከተቋም ገጽታ ግንባታ፣ ደንብ መተላለፎችን ከመከላከል እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር መልካም ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ ተቋሙ ከከተማዋ ልማትና እድገት ጋር አብሮ በማደግ ላይ ያለ ተወዳዳሪና የሌሎች ሚዲያ ተምሳሌት ለመሆኑን እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
ተቋሙ በኤኤምኤን ቴሌቭዥን ፣ በኤኤምኤን ፕላስ፤ በሬዲዮ፣ በሕትመት እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን በፍጥነት እና በጥራት ተደራሽ በማድረግ የብዙኃን አንደበት ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ቋንቋዎች መረጃዎችን ለአድማጭ ተመልካች እያቀረበ መሆኑን ገልጸው ሚዲያው ከተቋሙ ጋር በጋራ በመሆን ባከናወናቸው ስራዎች የባለስልጣኑን የግንዛቤ አድማስ ማስፋት የተቻለ መሆን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የአቀራረብ ይዘቱን በማሻሻል ይበልጥ ሳቢ በማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments