ባለስልጣኑ የህዳር ወር አፈፃፀሙን ገመገመ

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የህዳር ወር አፈፃፀሙን ገመገመ

ባለስልጣኑ የህዳር ወር  አፈፃፀሙን ገመገመ

            ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም 
            ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክ/ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር የህዳር ወር የስራ አፈፃፀሙን  ገመገመ::

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ ለተገኙት አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ መድረኩ የተዘጋጀው በስራ ሂደት የተገኙ መልካም ውጤቶችን ለማጠናከር ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል::

በመድረኩ ከማስፋፊያ እና ከመሀል ክ/ከተማ የተመረጡ ወረዳዎች ከጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 8, ኮ/ቀ ወረዳ 1 እና አራዳ ክ/ከ ወረዳ 1 የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ሪፖርት ቀርበዋል።

በእለቱ የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ በቁጥጥር ዘርፍ ላይ በማእከል ደርጃ እስከ ህዳር ማጠቃለያ የተከወኑ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል::

በመድረኩ  የባለስልጣኑ ዌብሳይት እና አጠቃቀሙ በተመለከተ በተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በአቶ ሚሊዮን ካሳሁን ተዋውቋል::

የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱት ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የባለስልጣኑ የበላይ ኃላፊዎች ምላሽ፣ማብራሪያና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል::

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው። 

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

የዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/

የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement

የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments