ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር የላቀ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
"ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር የላቀ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢን የመፍጠር እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የመልካም አስተዳደር ተምሳሌትነቱን ለማረጋገጥ በየደረጃው በሚገኙ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽህፈት ቤቶች የጀመራቸውን የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መተግበሩን አስታወቀ።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ቢሮውን በማዘመን ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር በአዲስ መልኩ ያደራጀውን ቢሮ የማስመረቅ እንዲሁም አዲሱ የፓራ ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ለተገልጋዮቹ የማስተዋወቅ መርሀ ግብር በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት አካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የክፍለ ከተማው የጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኦባድ ጁናን፣ የወረዳ የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት "ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር የላቀ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው" ካሉ በኋላ፣ በቀጣይም ይህ የሪፎርም ስራ ይበልጥ ተጠናክሮ በሌሎች ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ ተቋሙን ከተማዋ ከያዘችው የዘመናዊ ከተማነትና የልማት ጉዞ ጋር በማስተሳሰር ወደ ላቀ ከፍታ ማሸጋገር እንደሚገባም አሳስበዋል።
የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኦባድ ጁና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በአዲስ መልኩ የተደራጀውን ቢሮ እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አዲስ የደንብ ልብስ አስተዋውቀዋል።
ኃላፊው አክለውም ይህ ማሻሻያ በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥና መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ያለውን ፋይዳ ገልጸው፣ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ በሰንዳፋ እና በአዳይቱ በተሰጡ ስልጠናዎች ላይ ለተሳተፉ አካላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ክፍለ ከተማው ለሚያሳድጋቸው ህጻናትም የድጋፍና የስጦታ ማበርከት ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።
ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments