ባለስልጣኑ በ9995 ነጻ ስልክ መስመር በቀረቡ ጥቆማዎችና ቅሬታዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
ባለስልጣኑ በ9995 ነጻ ስልክ መስመር በቀረቡ ጥቆማዎችና ቅሬታዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
06/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት ከጥር 25 እስከ ሰኔ 30 2018 በነጻ ስልክ መስመር 9995 ከህብረተሰቡ የመጡ ጥቆማዎች ፣ ቅሬታዎች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የውይይት መድረክ አካሂዷል ።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ የህዝብ ጥቆማዎችንና ቅሬታዎችን በሰፊው ለማስተናገድ የ 9995 ነጻ የጥሪ ማዕከል ዘመናዊ በማድረግ ሙሉ በሙሉ በኮምፒውተር እንዲደራጅ ተደርጎ በ3 ፈረቃ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመሩንና ማዕከሉ የከተማዋን ነዋሪዎች ስብጥር ባገናዘበ መልኩ ጥቆማዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተቀብሎ ማስተናገድ የሚችሉ ባለሙያዎችን መድቦ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
በመድረኩ በጥቆማ የሚመጡ ቅሬታዎች በምን አግባብ ተፈቱ ያልተፈቱ ካሉ በቀጣይ ችግሮቹን በመለየት መፍትሔ መስጠት እንደሚገባና ከሚመለከተው ተቋም በመተባበር የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ም/ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።
በ2018 በጀት ዓመት ከ 25/05/2018 እስከ 30/10/2018 በነጻ ስልክ መስመር 9995 ከህብረተሰቡ የመጡ ጥቆማዎች ፣ ቅሬታዎች እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ሪፖርት ቀርቦ በመገምገም በቀጣይ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments