"ለተገልጋይ እና አገልጋይ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር የአገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ" እንደሚገባ ተገለጸ።
"ለተገልጋይ እና አገልጋይ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር የአገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ" እንደሚገባ ተገለጸ።
ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢን የመፍጠር እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የመልካም አስተዳደር ተምሳሌትነቱን ለማረጋገጥ በየደረጃው በሚገኙ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽህፈት ቤቶች የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በዛሬው እለት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰራውን የቢሮ ማዘመን ስራ ተመርቆ ለዘመናዊ አገልግሎት ዝግጁ አድርጓል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ቢሮውን በማዘመን ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር በአዲስ መልኩ ያደራጀውን ቢሮ የማስመረቅ እንዲሁም አዲሱ የፓራ ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ለተገልጋዮቹ የማስተዋወቅ መርሀ ግብር በዛሬው እለት አካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንዲሁም የ11ዱም ክ/ከተሞች ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ለተገልጋይና አገልጋዩ ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር የአገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ ያስፈልጋል በማለት በቀጣይም ይህ የሪፎርም ስራ ይበልጥ ተጠናክሮ በሌሎች ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ከማእከል ጀምሮ የዘመነ ተቋም መገንባቱን ገልጸው ወቅቱን የዋጀ በቴክኖሎጂ የታገዘ ብሎም ዘመናዊነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባደረጋቸው የሪፎርም ስራዎች እና በሚያከናውናቸው ተግባራቶች በከተማዋ የለውጥ አብነት መሆን ችሏል ለዚህም በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ተቋሙ ይሰነዘር የነበረውን አሉታዊ አመለካከት እንዲቀየር አድርጓል ብለዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ይህ የተቋም ለውጥ ፍሬያማ እንዲሆን የአማራሩና ሰራተኛው ውህደት ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጸው አሁንም በአገልግሎት አሰጣጥ ብሎም በሪፎርም ስራዎች ሞዴል ሆነን ተልእኮዎቻችንን በስኬት እንወጣለን ብለዋል።
የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኦባድ ጁና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በአዲስ መልኩ የተደራጀውን ቢሮ እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አዲስ የደንብ ልብስ አስተዋውቀዋል።
ኃላፊው አክለውም ይህ ማሻሻያ በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥና መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ያለውን ፋይዳ ገልጸው፣ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም በምረቃ ስነ ስረአቱ የታደሙት የየክ/ከተማደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊዎች ከአመራር ቁርጠኝነት ጨምሮ ጥሩ ተሞክሮ እንዳገኙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል
ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments