ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብነውን ድል አጠናክረን...

image description
- In code inforcement    0

ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብነውን ድል አጠናክረን ለማስቀጠል ዝግጁ ልንሆን ይገባል" — ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ

"ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብነውን ድል አጠናክረን ለማስቀጠል ዝግጁ ልንሆን ይገባል" — ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
     
              ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
                አዲስ አበባ     

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የነበረው ጥንካሬ ለማስቀጠል እና ክፍተቶች በማረም  የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀመጠ ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችንና ድሎችን በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው ለዚህ ውጤት መመዝገብ የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሩ ሚና ከፍተኛ እንደነበር በመጥቀስ በቀጣይም ለላቀ ስራ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በ2018 በጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራታቸው የመጡ ናቸው ፤ የደንብ መተላለፍን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራውን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ገልጸዋል።

​በቀጣይ በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና ብልሹ አሰራርን በጽናት በመታገል ህዝባዊ አገልግሎቱን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።

መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን በአግባቡ በመጠበቅና በመከላከል የመሬትን ወረራን መቶ በመቶ(100%) መቆጣጠር የተቻለበት መሆኑንና ሌሎች በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን እንዲቀንሱ በማድረግ በርካታ ተግባራት በበጀት ዓመቱ መከናወኑ በውይይቱ ተገልጿል።

ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ አመራር እና ሰራተኛ  በመናበብ እየሰራ እንደሚገኝና በዚህም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዘገቡንና በቀጣይም ይህን በማጠናከር የተሻለ ስራዎችን መስራት አንደሚገባ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል   ።

በበእለቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራቶች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተከናወኑ መፍትሔዎች ቀርበው ውይይት ተደርገውበታል።

በመድረኩ የክፍለ ከተማ አስተባባሪ፣ የቁጥጥር  ስራ አስተባባሪዎች፣ የግብረ ሀይል ቡድን መሪዎች እና የወረዳ ሽፍት መሪዎች ተገኝተዋል ።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments