በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዙሪያ ለበ...

image description
- In code inforcement    0

በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዙሪያ ለበጎ ፈቃደኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዙሪያ ለበጎ ፈቃደኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ 

                02 - 04 - 2017 ዓ.ም
                ***አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ "የደንብ መተላለፎችን መከላከል ለከተማችን እድገትና ውበት" በሚል መሪ ቃል ከ119 ወረዳ ለተወጣጡ የደንብ ማስከበር በጎ ፈቃደኞች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ። 

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሐመድ  ከህብረተሰቡ የተወጣጡ በጎ ፈቃደኞች ለተቋሙ አጋዥ ሀይል በመሆን የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገወጥ ድርጊቶችን ከኦፊሰሩ ጋር በጋራ  በመከላከልና በመቆጣጠር ውጤታማ ሰራዎችን ማከናወን መቻሉንና በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል ።

አክለውም በጎ ፈቃደኝነት ለህሊና እርካታ የሚከናወን ተግባር በመሆኑ ተቋሙን ማገዝ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመድረኩ የበጎ ፈቃደኞችን ለማስተዳደር የተዘጋጀ የአሰራር ማኑዋል እና የተሻሻለው የደንብ ቁጥር 167/2016 በባለስልጣኑ የኢንስፔክሽን ባለሙያ አቶ ተስፋሁን ታምሩ በዝርዝር ቀርቧል። 

በተጨማሪም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ምንነት፣ጽንሰ ሀሳብና ጠቀሜታ ከአዲስ አበባ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበር ኮሚሽን የስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሶፎንያስ ፍሰሀ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ። 

በቀረቡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ዙርያ   ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው ከተቋሙ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments