በከተማዋ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የሚደረጉ የተቀናጁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በከተማዋ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የሚደረጉ የተቀናጁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የቅመ መከላከል ስራዎች አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የግንዛዜ አሰጣጥ ስልቶች በተመለከተ የውይይት መድረክ ተካሄ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፈው በጀት ዓመት የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና በግምገማው የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና ብልሹ አሰራርን በጽናት በመታገል የምንሰጠውን አገልግሎት ማፋጠንና ህብረተሰቡን ዝቅ ተብሎ ማገልገል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንደገለጹት ባለፈው በጀት ዓመት በከተማዋ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የደንብ መተላለፍ ድርጊቶችን በቅድመ መከላከል ሥራዎች ለማስቀረት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በመሰራታቸው በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
በተቋሙ የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የቅድመ መከላከልና የስልጠና ሥራው ቁልፍ ሚና እንዳለው በመጠቆም በተያዘው በጀት ዓመትም የከተማዋን ጽዳት ውበትና ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተቀናጁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ ገልጸዋል ።
አክለውም በከተማችን የሚገኙ የህብረተሰብ አካላት የደንብ መተላለፍ እንዳይፈጽም እና እንዲጸየፍ ለማድረግ እየተሰጡ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
በመድረኩ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ የቅድመ መከላከልና የግንዛቤ ስራዎች ስራ የትኩረት አቅጣጫ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተቀምጠዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments