ባለስልጣኑ የእጩ አመራሮች የመሪነት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና መካሄድ ጀመረ
ባለስልጣኑ የእጩ አመራሮች የመሪነት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና መካሄድ ጀመረ
ሐምሌ 28/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ለተወጣጡ እጩ አመራሮች የመሪነት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና መካሄድ ጀምሯል።
ስልጠናው እንደ መሪ የማሰብ፣ የማቀድ እና የመፈጸም ክህሎትን ለማዳበር ያለመ ሲሆን በዋናነት የመሪነት ክህሎትን፣ የተከታይነት ባህሪያትን፣ የስሜት ብልህነትን፣ የመሪነት ንድፈ-ሀሳቦችን እና ስልቶችን፣ የማበረታቻ ስልቶችን እና ሌሎች ጠቃሚ የመሪነት ፅንሰ-ሀሳቦችን ያካተተ ነው።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በ2018 በጀት ዓመት በአፈጻጸሙ አንደኛ በመሆን የተሸለመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ስልጠና ከተማችን እያሳየች ያለችውን ፈጣን እድገት በሚመጥን መልኩ ተቋሙን በዘመናዊ አሰራር እና በእውቀት የሚመራ በተግባር የሚታይ የአመራር ብቃትን የተላበሰ፣ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ እና የአገልግሎት እርካታን የሚያረጋግጥ ብቁ እና ንቁ እጩ አመራሮችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ስልጠናው ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ በመግለጽ ሰልጣኞች ስልጠናውን በከፍተኛ ንቃት፣ ተነሳሽነት እና ጥብቅ ዲስፕሊን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
ይህ ስልጠና ተቋሙ የወደፊት ተተኪ መሪዎችን በማፍራት የተቋሙን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ ይህንን ስልጠና በማካሄድ ብቁ እና ንቁ አመራሮችን በማፍራት የከተማዋን እድገት ለማፋጠን እና የህዝብ አገልግሎትን ለማሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳኘ መሆኑ ተገልጿል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments