በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን ህግ የማስከበር...

image description
- In code inforcement    0

በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን ህግ የማስከበር ተልዕኳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ

"በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን ህግ የማስከበር ተልዕኳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ

             ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
               ** አዲስ አበባ**    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ ስራዎችን በየጊዜው በመገምገም ያለውን ጥሩ አፈፃፀም በማስቀጠል  የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ በማረም እንደሚሰራ ገለፁ።

በተለይ በክረምት ወራት የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የደም ልገሳ ንቅናቄዎች አበረታችና ውጤታማ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ተቋሙ ማንኛውም አሰራር ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ ሊሆን እንደሚገባ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለተገልጋዮችም ሆነ ለሰራተኞች ምቹና ተስማሚ የሥራ አካባቢ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

ህብረተሰቡም ከደንብ መተላለፍ እንዲቆጠብና የደንብ ማስከበር ስራው አጋዥ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን አጠናክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ።

በዚህ የእቅድ ጊዜ ውስጥ 20,000 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 608 ዩኒት ደም በመለገስ እና የአቅመ ደካሞች ቤቶችን በማደስ አበይት የበጎ አድራጎት ስራዎች ተከናውነዋል።

የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች 100% ጥበቃ የተደረገላቸው ሲሆን፣ ለከተማው ህብረተሰብ ሰፊ የግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች መከናወኑንና  በቀጣይም አሰራርን በዲጂታል (Smart Office) በማስደገፍ እና ቅሬታዎችን በ9995 የጥሪ ማዕከል በፍጥነት የመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ እቅዱን ያቀረቡት ኮለኔል አድማሱ አብራርተዋል። 

​በመጨረሻም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ90 ቀናት የልዩ ትኩረት ዕቅዱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል፣  የበጀት ዓመቱን የልማትና የደንብ ማስከበር ግቦች ስማርት አሰራሮችን በመተግበርና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በላቀ ሁኔታ እንደሚያስፈጽም ተገልጿል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments