
ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊ ተቋማትና ግለሰቦች በገንዘብ መቅጣቱ ገለፀ፡፡
ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊ ተቋማትና ግለሰቦች በገንዘብ መቅጣቱ ገለፀ
02/02/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ለማድረግ ቀንና ሌሊት እየሰራ ባለበት በዚህ ወቅት ደንብ በመተላለፍ የከተማው ውበት በግዴለሽነት የሚያበላሹ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የሚወስደውን የቅጣት እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ፀሀይ ግባት ኮንዶሚኒየም ግቢ የህብረተሰቡን ጤና በሚጎዳ መልኩ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢን በማቆሸሽ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት 100.000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቀጣታቸው የወረዳው የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አዳነ ገብሬ ገልፀዋል።
በተመሳሳይ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ያመነጩትን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ባለመያዝ እና የአካባቢውን ገፅታ በማበላሸት ኦምና አሳ ቤት 50,000 ብር፣ዘገየ ስጋ ቤት 50,000 ብር አናንያ ሆስፒታል 30,000 ብር በመቅጣት እርምጃ ተወስጿል።
በእለቱ በተደረገው ቁጥጥር ደንብ የተላለፉ ሌሎች ግለሰቦች በመቅጣት 169,000 ብር ለመንግስ ገቢ መደረጉን የወረዳው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ስሜነህ ይልቃል ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ ለከተማው ነዋሪዎች ማንኛውም የደንብ መተላለፎች ሲያጋጥሙ በነጻ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በማድረስ የከተማዋን ውበት እና ፅዳት እንዲጠበቅ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments