ባለስልጣኑ በ2019 በጀት አመት የደንብ መተላለ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በ2019 በጀት አመት የደንብ መተላለፎችን በ54.3 ፐርሰንት ለመቀነስ ማቀዱ ተገለፀ

ባለስልጣኑ በ2019 በጀት አመት የደንብ መተላለፎችን በ54.3 ፐርሰንት  ለመቀነስ ማቀዱ ተገለፀ

14/12/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2019 በጀት አመት እቅድ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከል ሰራተኞች ጋር የተቋሙ ስኬት በማስቀጠል የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ በተነደፉ ስልቶች እና እቅዶች ላይ ውይይት ተደረገ።

በውይይቱን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ2019 በጀት አመት የቀደውን እቅድ በትጋትና በቁረጠኝነት በመስራት በከተማችን የደንብ መተላለፍ እንዲቀንስና በተነደፉ ስልቶች እና እቅዶች መሠረት በትጋት በመፈፀም በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ሁሌም ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በበጀት ዓመቱ የደንብ መተላለፍ የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንደሚሰጡና በቴክኖሎጂ በታገዘ የደንብ መተላለፍ በመከላከል በመቆጣጠር በ9  የደንብ መተላለፎች ላይ በ54.3 ፐርሰንት ለመቀነስ መታቀዱ ተናግረዋል።

በቀጣይ ከሁለት ሺህ በላይ አዲስ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን መልምሎ ስልጠና በመስጠት ወደ ተቋሙ በመቀላቀል እና በስራ ላይ ያሉትን ከ7000 በላይ ነባር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰር በማስልጠን የሰው ሃይሉ ለማብቃት እንደሚሰራ በተነደፈው ስልት ተመላክቷል።

በመድረኩ በ2018 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዳይሬክተሮች ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ምስጋናና እውቅና በመስጠት ለመላው የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማ ደረጃ 1ኛ እንዲወጣና ተሸላሚ እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments