የአዲስ አበባ ከተማ ውበት ለማስጠበቅና የደንብ...

image description
- In code inforcement    0

የአዲስ አበባ ከተማ ውበት ለማስጠበቅና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የህብረተሰቡ ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ውበት ለማስጠበቅና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የህብረተሰቡ ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ      

            ነሐሴ 21 /2018 ዓ.ም
                **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን "የተቋሙን ስኬቶች ለማስቀጠል የህብረተሰቡ ድርሻ የላቀ ነው  " በሚል መሪ ቃል  ከተማ አቀፍ የህዝብ ውይይት  መድረክ አካሄደ።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባሳለፍነው በጀት ዓመት በርካታ የደንብ ጥሰቶችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀው የተመዘገቡት ስኬቶች በሙሉ የህብረተሰቡና የባለድርሻ አካላት ጠንካራ አጋርነት ውጤት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የደንብ ማስከበር ተልዕኮውን አጠናክሮ በመቀጠል፣ በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰር በመገንባትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህዝቡን እርካታ ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በመድረኩ የውይይት መነሻ የባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ እና ለከተማው ነዋሪዎች ቀርቧል።

ተቋሚ  በቀጣይ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎትና  አሰራርን በመዘርጋት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት  በትኩረት እንደ ሚሰራ ገልጸዋል።

በቀጣይ እቅዱ የህዝብ ተሳትፎንና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ይበልጥ በማጠናከር የደንብ መተላለፎችን በመከላከልና ለመቀነስ እንደሚሰራ ተመላክቷል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በየአካባቢአቸው የደንብ መተላለፎች በመከላከልና የአከባቢያችንን እንዲሁም የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅና ደንብ በማስከበር ከተቋሙ ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments