የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ

           ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም
               **ሐረር**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልዑካን ቡድን አባላት ከሐረር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።

በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር መሠረተ ልማት ጥበቃና የደንብ መቸላለፎች ቅድመ መከላከል እና ቁጥጥር
አስመልክቶ ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮው  የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሳ አልዮ እና የተቋሙ ሰራተኞች አጋርተዋል።

በልምድ ተሞክሮ ልውውጡ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር  አሰራሮች እና ተሞክሮዎች የሐረሬ ከተማ አስተዳደር  ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ  ውጤት ማምጣት መቻሉን  ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ ከመቅጣት ይልቅ በቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት አድርግው ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ለልዑካን ቡድን አባላቱ የሐረሪ ክልል የደንብ ማስከበር ፅ/ኃላፊ  አቶ ኢብሳ አልዪ፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች  እና የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ተገኝተው አቀባበል አድርገው ልምድና ተሞክሮአቸው አጋርተዋል።

መረጃው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments