በአዲስ አበባ ከተማ የኮርደር መሠረተ ልማት ጥ...

image description
- In code inforcement    0

በአዲስ አበባ ከተማ የኮርደር መሠረተ ልማት ጥበቃ የጋራ ጥምር ግብረ-ሀይል ሊቆጠር የሚችል ውጤታማ ስራዎች መስራቱ ተገለፀ፡፡


         በአዲስ አበባ ከተማ የኮርደር  መሠረተ ልማት ጥበቃ የጋራ ጥምር ግብረ-ሀይል   ሊቆጠር የሚችል ውጤታማ ስራዎች መስራቱ ተገለፀ

           ታህሳስ 3/4/2017 ዓ.ም
            ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ  ከተማ አስተደደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ የትራፊክ ማነጅመንት ባለስልጣን ፣  የግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን  ፣ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር  ባለስልጣን  ከፍተኛ አመራሮች  በተገኙበት የኮሪደር መሰረት ልማት ጥብቅ የጋራ ጥምር ግበረሀይል የ5 ወራት የስራ አፈፃፀመ  በሳሬም ሆቴል ግምገማ አካሂዷል።

በግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻ ንግግራቸው አዲስ አበባን ውብ ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና እንደስሟ አበባ ለማድረግ  5 ጥምር ተቋማት በኮሪደር ልማቱ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ቀን ከለሊት እጅ ለእጅ በመያያዝ ተጨባጭና ሊቆጠር የሚችል ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣንም አዲስ  በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ.ም እና በኮሪደር ልማቱ ጥበቃ ዙርያ  በ5ወራት በመድረክ ፣ በመንገድ ላይ እና በቤት ለቤት በርካታ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራቱን ገልፀዋል፡፡

በኮሪደር ልማቱ ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ያልሆኑ መንገዶች እንደተስተካከሉና አዳዲስ መንገዶችም በመሰራታቸው  አደጋዎች መቀነሳቸውን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ስራ  አስኪያጅ አቶ  ክበበው ሜዴቅሳ ናቸው ፡፡

አያይዘውም በኮሪደር ልማቱ ህግ በመተላለፍ 38.8 ሚሊዮን ብር በትራፊክ ማኔጅመት የቅጣት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

በኮሪደር መሰረት ልማት ጥብቅ የጋራ ጥምር  ግብረ ሀይል በ5ወራት የተሰሩ ስራዎችን  አስመልክቶ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን የለውጥና ስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀፀላ የውይይት መነሻ የሚሆን ሪፖርት ቀርቧል ፡፡

በቀረበው ሪፖርት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን  በ5 ወራት ከ266 ድርጅት ከ19,061 ግለሰቦች በድምሩ 103 ሚሊዮን ብር የማስተማሪያ ቅጣት በመቅጣት ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ማድረጉን ተጠቅሷል ፡፡ 

በዕለቱ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር  ባለስልጣን ፣የፅዳትና አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ የትራፊክ መኔጅመንት ባለስልጣን እና  የግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር  ኃለፊዎች በጥምር ግብረ ሀይሉ የሰሩትን ስራዎች አስመለክቶ  ገለፃ አድርገዋል፡፡

በቀረበው የሰራ አፈፃፀም ዙርያ   ከተሳታፊዎች ጋር  ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ከተሳታፊዎች ተነስተው ከመድረክ ከ5ቱም ተቋማት አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው  መድረኩ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments