ባለስልጣኑ በመስከረም ወረ የሚከበሩ በዓላት ምክንያት በማድረግ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎች በስልታዊ የመከላከል እና የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ ገለፀ
ባለስልጣኑ በመስከረም ወረ የሚከበሩ በዓላት ምክንያት በማድረግ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎች በስልታዊ የመከላከል እና የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ ገለፀ
መስከረም 05/2019 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመስከረም ወር ዕቅድና ወቅታዊ የመዲናዋን የደንብ ማስከበር ስራዎች በተመለከተ ከፍተኛ አመራሮች ከዘርፍ ዳይሬክተሮች ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደ ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባደረጉት ንግግር ይህ ውይይት በተቋሙ የታዩ ጠንካራ ጎኖችንና ክፍተቶችን በጥልቀት ለመፈተሽ የሚያስችል በመሆኑ በቀጣይ ስራዎች ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ እንዲከናወኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
አክለውም ዕቅዶችን በየጊዜው ገምግሞ ማየት ለተቋማዊ ስራዎች መሳካት ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም የመስከረም ወር የበርካታ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት እንደመሆኑ መጠን የከተማዋን ሰላምና ጽዳት ለማስጠበቅ የተቀናጀ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ክትትል፣ ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ፣ የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ እንዲሁም የድጋፍ ሰጪ ዘርፍ በወሩ ለማከናወን ያቀዷቸውን መደበኛ ተግባራት፣ የቁጥጥር ስልቶችን ፣ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እና ወቅታዊ የደንብ ማስከበር ስራዎችን ዝርዝር ዕቅድ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ፣ ፈጣን እና ዘመናዊ ማድረግ እንደሚገባ እንዲሁም የቅንጅት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል ።
መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments